የጨጓራ ህመም መንስኤ እና መፍትሄ/Gastritis

የጨጓራ ህመም መንስኤ እና መፍትሄ/Gastritis
ስንቶቻችን ስለ ጨጓራ ህመም አስከፊነት እናውቃለን?ስንቶቻችንስ ህመሙን ቸል እንለዋለን?በ ጊዜው ካልታከመ ለጨጓራ ካንሰር እንደሚዳርግስ ያውቃሉ?መቼ ወደ ጤና ተቋም መሄድ እንደለብዎስ? ዛሬ እነሆ እንደተለመደው ዶክተር አለ 8809 ልትረዱት ስለሚገባው የጨጓራ ህመም እንካችሁ ብሏል
የጨጓራ ግድግዳዎች መቅላት፣ ማቃጠል እና መቁሰል የጨጓራ ህመምን ያስከትላል በሽታው በድንገት ወይም በጊዜ ብዛት ሊከሰት ይችላል።
✔በሽታው እንዴት ይከሰታል?
የጨጓራ በሽታ በሚከተሉት መመንስኤዎች ይከሰታል፦
※ በአልኮል ምክንያት በሚከሰት የማቃጠል ስሜት
※ በከባድ ማስታወክ
※ ከባድ ጭንቀት/ብስጭት
※ በአንዳንድ መድሃኒቶች ለምሳሌ አስፕሪን ሊከሰት ይችላል።
በተጨማሪም በሚከተሉት መንስኤዎች ይከሰታል፦
※ ሄሊኮባክተር ፓይሎሪ(h.pylori)
ይህ የጨጓራ ባክቴሪያ ሲሆን በጨጓራ ንፍጣማ ግድግዳዎች ላይ ይኖራል/ይቀመጣል። በጊዜ የማንታከመው ከሆነ ከሆነ ወደ ጨጓራ ቁስለት በአንዳንድ ሰዎች ላይ ደግሞ የጨጓራ ካንሰር ሊከሰት ይችላል።
※ ፐርኒሺየስ አኒሚያ
የደም ማነስ ዓይነት ሲሆን ቫይታሚን ቢ12 ለመፍጨትና ለመምጠጥ የሚያገለግል የተፈጥሮ ንጥረ ነገር በጨጓራ ውስጥ ሳይኖር ሲቀር ይከሰታል።
※ የሀሞት መፍሰስ
ሀሞት ወደ ጨጓራ ከሀሞት ከረጢት ተመልሶ በሚፈስበት ጊዜ ሊከሰት ይችላል።
※ በባክቴሪያና ቫይረስ በሚፈጠር ኢንፌክሽን
✔የጨጓራ ህመም ምልክቶች
የጨጓራ በሽታ ምልክቶች ከሰው ወደ ሰው የሚለያዮ ሲሆን በአንዳንድ ሰዎች ላይ ምንም ዓይነት ምልክት ላይታይባቸው ይችላል። በጣም የተለመድና በብዙ በሽተኞች ላይ የሚታዮ ምልክቶች እነሆ፦
※ የማቅለሽለሽ ስሜት
※ የሆድ ህመም
※ የሆድ መነፋት
※ ማስታወክ
※ የምግብ አለመፈጨት
※ የማቃጠል ወይም የማግሳት ስሜት በምግብ ሰዓት አካባቢ ወይም በማታ ሰዓት
※ ስቅታ(ስርቅታ)
※ የምግብ ፍላጐት መቀነስ
※ የደም ወይም የቡና ቀለም ያለው ትውከት
※ ጥቁር ቀለም ያለው ዓይነ ምድር ናቸው።

የሚወሰድ መከላከያዎች እና መድሃኒቶች

※ የጨጓራ አሲድ መጠንን ለመቀነስ ፀረ አሲድ(Anti Acid) ወይም ሌሎች መድሃኒቶችን መውሰድ።
※ ትኩስና ቅመማ ቅመም ያላቸውን ምግቦች አለመመገብ።
※ በባክቴሪያ ምክንያት ለሚከሰት የጨጓራ በሽታ ፀረ ባክቴሪያ እና የጨጓራ አሲድ ምርትን የሚቀንሱ መድሃኒቶች ያታዘዙለታል።
※ በፐርኒሺየስ የደም ማነስ የተከሰተ የጨጓራ በሽታ ከሆነ ቫይታሚን ቢ12 እንዲወስድ ይደረጋል።
※ የጨጓራ መቃጠልን የሚያስከትሉ ምግቦችን መውሰድ ማቆም።
በመጨረሻም የጨጓራ ህመምን የሚቀሰቅሱ/የሚያስነሱ ምክንያቶችን ካወቅን እነዚህ ነገሮችን ባለመጠቀም ከህመሙ በቀላሉ ማገገም ይቻላል። በተጨማሪም በጨጓራ በሽታ የተያዙ ሰዎች ህክምና ከጀመሩ በኃላ በፍጥነት ከህመማቸው ያገግማሉ።
t.me/josilo

تعليقات

إرسال تعليق

تعليقات خورزراف

المشاركات الشائعة من هذه المدونة

قصة حقيقية حدثت بين صديقين

الأنبياء والمرسلين قصص الانبياء والرسل

هل تسبيح حرام او حلال