የጨጓራ ህመም መንስኤ እና መፍትሄ/Gastritis
የጨጓራ ህመም መንስኤ እና መፍትሄ/Gastritis ስንቶቻችን ስለ ጨጓራ ህመም አስከፊነት እናውቃለን?ስንቶቻችንስ ህመሙን ቸል እንለዋለን?በ ጊዜው ካልታከመ ለጨጓራ ካንሰር እንደሚዳርግስ ያውቃሉ?መቼ ወደ ጤና ተቋም መሄድ እንደለብዎስ? ዛሬ እነሆ እንደተለመደው ዶክተር አለ 8809 ልትረዱት ስለሚገባው የጨጓራ ህመም እንካችሁ ብሏል የጨጓራ ግድግዳዎች መቅላት፣ ማቃጠል እና መቁሰል የጨጓራ ህመምን ያስከትላል በሽታው በድንገት ወይም በጊዜ ብዛት ሊከሰት ይችላል። ✔በሽታው እንዴት ይከሰታል? የጨጓራ በሽታ በሚከተሉት መመንስኤዎች ይከሰታል፦ ※ በአልኮል ምክንያት በሚከሰት የማቃጠል ስሜት ※ በከባድ ማስታወክ ※ ከባድ ጭንቀት/ብስጭት ※ በአንዳንድ መድሃኒቶች ለምሳሌ አስፕሪን ሊከሰት ይችላል። በተጨማሪም በሚከተሉት መንስኤዎች ይከሰታል፦ ※ ሄሊኮባክተር ፓይሎሪ(h.pylori) ይህ የጨጓራ ባክቴሪያ ሲሆን በጨጓራ ንፍጣማ ግድግዳዎች ላይ ይኖራል/ይቀመጣል። በጊዜ የማንታከመው ከሆነ ከሆነ ወደ ጨጓራ ቁስለት በአንዳንድ ሰዎች ላይ ደግሞ የጨጓራ ካንሰር ሊከሰት ይችላል። ※ ፐርኒሺየስ አኒሚያ የደም ማነስ ዓይነት ሲሆን ቫይታሚን ቢ12 ለመፍጨትና ለመምጠጥ የሚያገለግል የተፈጥሮ ንጥረ ነገር በጨጓራ ውስጥ ሳይኖር ሲቀር ይከሰታል። ※ የሀሞት መፍሰስ ሀሞት ወደ ጨጓራ ከሀሞት ከረጢት ተመልሶ በሚፈስበት ጊዜ ሊከሰት ይችላል። ※ በባክቴሪያና ቫይረስ በሚፈጠር ኢንፌክሽን ✔የጨጓራ ህመም ምልክቶች የጨጓራ በሽታ ምልክቶች ከሰው ወደ ሰው የሚለያዮ ሲሆን በአንዳንድ ሰዎች ላይ ምንም ዓይነት ምልክት ላይታይባቸው ይችላል። በጣም የተለመድና በብዙ በሽተኞች ላይ የሚታዮ ምልክቶች እነሆ፦ ※ የማቅለሽለሽ ስሜት ※ የሆድ ህመም ※ የሆድ መነፋት ※ ማስታወክ